በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለአማራና አፋር ተረጅዎች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ ሰጠች

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተጠሪ አምባሳደር ትሬሲ ኤ ጃኮብሰን ለዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት /IOM/፣ ለአማራ እና አፋር ሰብአዊ ድጋፍ እኤአ መጋቢት 9 ቀን 2022 በተካሄደበት ወቅት መግለጫ ሲሰጡ።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተጠሪ አምባሳደር ትሬሲ ኤ ጃኮብሰን ለዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት /IOM/፣ ለአማራ እና አፋር ሰብአዊ ድጋፍ እኤአ መጋቢት 9 ቀን 2022 በተካሄደበት ወቅት መግለጫ ሲሰጡ።

ዩናይትድ ስቴትስ ለአፋርና አማራ ክልል የሚውል የ250 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ በኢትዮጵያ ለሚገኘው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ማስረከቧን በኢትዮጵያ የሚገኘው ኤምባሲዋ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት ተጎጂ ለሆኑ በ10ሺዎች ለሚቆጠሩ ተረጅዎች የሚሰጠውን አስቸኳይ እርዳታ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የ(IOM) ተጠባባቂ ኃላፊ ጂያን ዛሆ እና ለኢትዮጵያ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል አስተዳደር ረዳት ኮሚሽነር ነቢዩ ያሲን ያስረከቡት በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ትሬስ ኤ ጃካብሰን መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

በኢትዮጵያ የየዩናይትድ ኤምባሲ ተጠሪ አምባሳደር ትሬሲ ኤ ጃኮብሰን፣ የአይኦኤም ተጠባባቂ ኃላፊ ጂያን ዣኦ፣ ኢትዮጵያ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል አስተዳደር ምክትል ኮሚሽነር ነቢዩ ያሲን እና የዩኤስኤአይዲ የኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር ጀምስ ዶብሰን የአሜሪካ ኤምባሲ ለአይኦኤም የሰብአዊ አቅርቦቶችን ርክክብ ላይ ተገኝተዋል። ለአማራ እና አፋር በአዲስ አበባ በሚገኘው የIOM መጋዘን እኤአ መጋቢት 9 ቀን 2022 ዓ.ም.

እርዳታው ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያውጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች የሚገኙበት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ወደ አስር ሺህ የሚቆጠሩ ብርድ ልቦስች የጤና መጠበቂያዎች የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በ(IOM) አማካይነት በሰሜን ኢትዮጵያ በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖች እርዳታ ስትስጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑንና ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ለመሰጥት ቃል ከገባቸው የ900 ሚሊዮን ዶላር የሰብአዊ እርዳታ ተጨማሪ መሆኑን በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ አመልከቷል፡፡

አምባሳደር ጃኮብሰን በሰጡት መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ላለፉት 17 ወራት ከኢትዮጵያውያን እና ከአጋሮችዋ ጋር በመሆን አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ ያለመታከት መስራቷንም ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማትና የእርዳታ ድርጅት ዩኤስኤድ USAID በአስር ሺህዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች መሠረታዊ እርዳታው እንደሚያጓጉዝ አምባሳደሩ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በግጭት እንዲሁም እንደ ድርቅና የዝናብ እጥረት በመሳሰለው አየር ንብረት ቀውስ ወደ 4.2 ሚሊዮን የሚቆጠሩ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መኖራቸውን የ(IOM) ተጠባባቂ ኃላፊ ጂያን ዛሆ እና ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG