በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓኪስታን  የጦር ሠፈር በደረሱ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ


ፓኪስታን ባኑ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል የነፍስ አድን ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች በቦምብ ፍንዳታ ጉዳት የደርሰባቸውን ሲረዱ ያሳያል፣ የካቲት 25፣ 2017 ዓ.ም.
ፓኪስታን ባኑ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል የነፍስ አድን ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች በቦምብ ፍንዳታ ጉዳት የደርሰባቸውን ሲረዱ ያሳያል፣ የካቲት 25፣ 2017 ዓ.ም.

በፓኪስታን ወታደራዊ ካምፕ በደረሱ ሁለት የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች ሲሞቱ 25 ቆስለዋል ሲሉ ባለሥልጣናትና የሆስፒታል ኃላፊዎች አስታወቁ።

ጥቃቶቹ የደረሱት አጥቂዎች በሰሜን ምዕራብ ፓኪስታን ባኑ የሚገኘውን የጦር ሠፈር አጥር ጥሰው በመግባት ባደረሱት የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት እና ግቢውን በወረሩ ታጣቂዎች መሆኑን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ከጦር ሠፈሩ አጥር አቅራቢያ ሁለት የአጥፍቶ ጠፊዎቹ ቦምቦቹ የፈነዱ ሲኾን ወደ ውስጥ ለመግባት የሞከሩ ከአምስት እስከ ስድስት የሚደርሱ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን ያልገለጹ ባለሥልጣናትን ተናግረዋል።

ከፓኪስታኑ ታሊባን ጋራ ግንኙነት ያለው ቡድን በከይበር ፓኪስታኗ ባኑ ግዛት ውስጥ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዷል። በጥቃቱ በርካታ የፓኪስታን የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውንም ቡድኑ አስታውቋል።

ወታደራዊ ኃይሉ በሰው ህይወት ላይ የደረሰውን ጉዳት አላረጋገጠም። ነገር ግን የባኑ ወረዳ ሆስፒታል አራት ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን ተናግሯል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ጀምበር ከጠለቀች በኋላ ሰዎች የዕለቱን የረመዳን ጾም ለመፍታት በዝግጅት ላይ እንዳሉ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

አጥቂዎቹ ባኑ ከተማ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን መፈጸማቸው ተገልጿል። ባለፈው ኅዳር ወር በአጥፍቶ ጠፊ በተጠመደ የመኪና ቦምብ 12 ወታደሮች ሲገደሉ በደኅንነት ጣቢያው ላይ የነበሩ በርካታ ሰዎች ቆሰለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG