በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፊሊፒንስ መስጊድ ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጡ


ዛሬ በደቡባዊ ፊሊፒንስ በሚገኝ መስጊድ ላይ በተፈፀመ የፈንጂ ጥቃት ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ዛሬ በደቡባዊ ፊሊፒንስ በሚገኝ መስጊድ ላይ በተፈፀመ የፈንጂ ጥቃት ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በሙስሊሙ ክልል የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲኖር በህዝበ ውሳኔ ከፀደቀ በኋላ በመስጊድ ላይ ህይወት ያጠፋ ጥቃት ሲፈፀም ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

ጥቃቱ ማለዳ ላይ የተፈፀመው ዛምቦአንጋ በተባለች ከተማ ሲሆን አራት ሰዎች እንደቆሰሉ ታውቋል።

ጆሎ በተባለው ቦታ ላይ ለተፈፀመው ጥቃት እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ፅንፈኛ ቡድን ኃላፊነት ወስዷል። የክልሉ ባለሥልጣኖች ግን የአቡ ሰያፍ ሥራ ነው ይላሉ። እስላማዊ መንግሥት ነኝ ለሚለው ቡድን ታማኝነቱን የገለፀው የአቡ ሳያፍ ኃይል ለአስርተ ዓመታት ያህል ሲያካሄድ በቆየው አመፅ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቦምብ ጥቃቶች አካሂዷል፣ አንገት ሲቀላና የጠለፋ ተግባርም ሲፈፅም ኖሯል ተብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG