ዋሺንግተን ዲሲ —
ህንድ፣ ሙምባይ ውስጥ እአአ በ1993 ለደረሰውና ከ250 በላይ ሰዎች ላለቁበት ፍንዳታ ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ሁለት ሰዎች በሞት እንዲቀጡ፣ አንድ የህንድ ፍርድ ቤት ዛሬ ሐሙስ በየነባቸው።
ፌሮዝ አብዱል ራሺድ ካሃን እና ታሂር መርቸንት የሞት ቅጣት የተበየነባቸው፣ በፍንዳታው ተመሳጥረው በመገኘታቸው መሆኑም ተገልጧል።
ሦስተኛውና በጥቃቱ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል የተባለው አቡ ሰላም ደግሞ በዕድሜ ይፍታህ፣ ዓለም በቃኝ ወርዷል።
ይህ ግለሰብ ከጥቃቱ በኋላ አገር ጥሎ ጠፍቶ እንደነበር፣ የሞት ቅጣት እንደማያገኘው ስምምነት በመደረሱ ግን፣ እአአ በ2005 ከፖርቹጋል ወደ ህንድ መመለሱ ታውቋል።
ዓቃቤ ህግ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት፣ በሌላ አምስተኛ ተከሳሽ ላይም የ10 ዓመት እስራት እንዳስፈረደ ታውቋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ