በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይሮቢ ከ7 ዓመት በፊት በደረሰው ፍንዳታ 2ሰዎች ላይ ተፈረደ


ሞሐመድ አሕመድ አብዲና ሑሴን ሐሰን ሙስጠፋ
ሞሐመድ አሕመድ አብዲና ሑሴን ሐሰን ሙስጠፋ

ከሰባት ዓመታት በፊት ናይሮቢ በሚገኝ የገበያ ማዕከል ቢያንስ 67 የሚሆኑ ሰዎችን የገደሉትን እስላማዊ አማጽያን ረድተዋል በሚል ክስ ሁለት ሰዎች ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸውን አንድ የኬንያ ፍርድ ቤት በይኗል።

ሞሐመድ አሕመድ አብዲና ሑሴን ሐሰን ሙስጠፋ የተባሉት ሰዎች አሸባሪ ተግባር ለመፈጸም በማሴር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። አንድ ሦስተኛ ሰው ግን በነፃ ተለቋል ተብሏል። ከሰባት ዓመታት በፊት መስከረም ወር ላይ ዌስት ጌት በተባለው የገበያ ማዕከል ላይ ለተፈፀመው ጥቃት፣ ተጠርጣሪዎች ለፍርድ ሲቀርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ጥቃቱን የፈፀሙት የሶማሊይ ጽንፈኛ ቡድን አል ሸባብ አባላት መሆናቸው ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG