በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን በተካሄደ ሰልፍ ሁለት ጋዜጠኞች ተደበደቡ


ትናንት ማክሰኞ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ውስጥ በተካሄደ ሰልፍ፣ ሁለት ጋዜጠኞች በአፍቃሪ መንግሥት ተቃዋሚዎች ተደበደቡ።

ትናንት ማክሰኞ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ውስጥ በተካሄደ ሰልፍ፣ ሁለት ጋዜጠኞች በአፍቃሪ መንግሥት ተቃዋሚዎች ተደበደቡ።

በተለይ አንድ የምዕራብ አገር ጋዜጠኛ ክፉኛ እንደተደበደበ ተገልጧል።

ወደ ደቡብ ሱዳን የሚደረገውን የጦር መሣሪያ ዝውውር ለመገደብ ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ሳምንት ያሳለፈችውን ውሳኔ ለመቃወምና ለማውገዝ በተካሄደ ሰልፍ ወጣቶችን፣ ሴቶችንና የጎሣ መሪዎችን ያካተተ በመቶዎች የሚቆጠር ሕዝብ ተካፋይ እንደነበርም ታውቋል።

ትዕይንተ ሕዝቡን ያስተባበረው የደቡብ ሱዳን ካውንስል ኦፍ ቺፍስ ሲሆን፣ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላትም፣ ሕዝቡ ይህን የዩናይትድ ስቴትስን ውሳኔ እንዲቃወም ከተማው ውስጥ በመኪና እየተዘዋወሩ ቅስቀሳ ማካሄዳቸው ተነግሯል።

የዓይን ምስካሪዎች እንደገለፁት፣ በዚህ ጁባ አየር ማረፊያ አጠገብ በሚገኘው የተመድ ሚሽን ደጃፍ ላይ በተካሄደው ተቃውሞ የተካፈሉ ወጣቶች፣ ቁጣና ንዴታችውን በጋዜጠኞች፣ ይልቁንም በውጪ ጋዜጠኞች ላይ ለመወጣት ሲሞክሩ ተስተውለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG