በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞችን ገድለዋል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎች ታሰሩ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ሁለት የሁንዳራስ ተወላጅ ወጣት ፍልሰተኞችን ገድለዋል በሚል ተጠርጥረው ሦስት ስዎች ሜክሲኮ ውስጥ ታስረዋል። ልጆቹ ባለፈው ቅዳሜ ቲዋና በተባለችው የድንበር ከተማ ሞተው ተገኝተዋል።

ሁለት የሁንዳራስ ተወላጅ ወጣት ፍልሰተኞችን ገድለዋል በሚል ተጠርጥረው ሦስት ስዎች ሜክሲኮ ውስጥ ታስረዋል። ልጆቹ ባለፈው ቅዳሜ ቲዋና በተባለችው የድንበር ከተማ ሞተው ተገኝተዋል።

ዓቃብይነ ህግ ባወጡት መግለጫ መሰረት ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት በግድያና በሌሎች ክሶች ተጠርጥረው ተይዘዋል። ሟቾቹ የ16 እና የ17 ዓመት ዕድሜ ወጣቶች ሳይሆኑ እንዳልቀረ መግለጫው ጠቁሟል።

ልጆቹ ከመጠለያ ሰፈር ወጥተው መንገድ ላይ ሲሄዱ ሌቦች የሚመስሉ ስዎች እንዳስቆሟቸውና አንደኛው ከነሱ ጋር የነበረ ልጅ ጉዳት ቢደርስበትም እንዳመለጠ፤ የሁለቱ ልጆች አስከሬኖች ግን ታንቀውና በሰለት ተወግተው እንደተገኙ መግለጫው ገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG