በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመቱ ያሉ ሁለት የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች በደቡብ አፍሪካ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ባሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፍጥነት የሚዛመቱ ሁለት የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች መኖራቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ከአፍሪካ ሃገሮች ሁሉ በኮቪድ-19 በከፋ ደረጃ የተጠቃችው ደቡብ አፍሪካ ሊከሰት ለሚችለው አዲስ የከበደ የቫይረሱ ሥርጭት ተዘጋጅታለች።

የደቡብ አፍሪካ የተላላፊ በሽታዎች ብሄራዊ ተቋም ባለሥልጣናት “ቢ.1.617.2” እና “ቢ.1.1.7” በሚል ስያሜ የሚጠሩት የቫይረሱ ዝርያዎች የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ትናንት ይፋ አድርገዋል።

አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን የተረጋገጡ የቫይረሱ ተጋላጮች የተገኙባት እና 55,000 ህሙማን ለህልፈት የተዳረጉባት ደቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ ትልቁን ቁጥር ይዛለች።

ህንድ ውስጥ ባሁኑ ወቅት እየተዛመተ ባለው የቫይረሱ ዝርያ የተያዙ አራት ሰዎች ተገኝተ ተለይተው እንዲቆዩ መደረጉንና ከነሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች እየተፈለጉ መሆኑን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።

ባሁኑ ወቅት ከህንድ በሚገቡ ተጓዦች ላይ የሚወሰዱ የምርመራ ናሙናዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እያደረግን ነን ብለዋል እንዲሁም መጀመሪያ ላይ እንግሊዝ ውስጥ በተከሰተው ዝርያ የተያዙ አስራ አንድ ሰዎች መገኘታቸውን ገልጸዋል፤ ህዝቡ በከፍተኛ ንቃት ራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG