በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቴላቪቭ ጎዳና ላይ በተፈጠረ ፀብ ሁለት ኤርትራውያን መገደላቸውን የእስራኤል ፖሊስ አስታወቀ


በቴላቪቭ ጎዳና ላይ በተፈጠረ ፀብ ሁለት ኤርትራውያን መገደላቸውን የእስራኤል ፖሊስ አስታወቀ
በቴላቪቭ ጎዳና ላይ በተፈጠረ ፀብ ሁለት ኤርትራውያን መገደላቸውን የእስራኤል ፖሊስ አስታወቀ

በኤርትራ ያለውን መንግስት በሚደግፉ እና በሚቃወሙ ኤርትራውያን መካከል የእስራኤል የንግድ ማዕከል በሆነችው ቴል አቪቭ ጎዳና ላይ ቅዳሜ እለት በተፈጠረ ጸብ ሁለት ኤርትራውያን መሞታቸውን የእስራኤል ፖሊስ አስታወቀ።

ኤርትራዊያኑ ቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኘው 'ሀግና' ጎዳና ላይ ድንጋይ በመወራወር ባካሄዱት ግጭት ስምንት ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ጨምሮ ገልጿል።

መግለጫው አክሎ፣ የሕክምና አካላትን እንደምንጭ በመጥቀስ "በግጭቱ ሁለት ኤርትራውያን ህይወታቸው አልፏል" ብሏል።

የፖሊስ መግለጫ ሁለቱ ሰዎች እንዴት እንደሞቱ ባያብራራም፣ የእስራኤል ሚዲያዎች ግን በስለት ተወግተው መቁሰላቸውን ዘግበዋል። ፖሊስ በወንጀሉ ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን አመልክቷል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያዊዎች እስራኤል ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ከአመታት በፊት በግብፅ ቀይ ባህር እና በሜዲትራኒያን ባህር መካከል የሚገኘውን በረሃ አቋርጠው የገቡ ናቸው።

እ.አ.አ በ2023 በሁለቱ ተቀናቃኝ የኤርትራ ቡድኖች መካከል በተነሳ ተመሳሳይ ግጭት፣ ፀቡን ለማብረድ የሞከሩ የእስራኤል ፖሊሶችን ጨምሮ ከ12 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG