በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮንጎ ውስጥ የኢቢላ ወረርሽኝን በማጥፋ ሥራ ላይ የተሰማሩ ተገደሉ


ኮንጎ ውስጥ የኢቢላ ወረርሽኝን በማጥፋ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሁለት የማኅበረብ ጤና ሠራተኞች፣ ምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ክፍለ-ሀገር ኬቬዮ ውስጥ መገደላቸውን፣ የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ ሰኞ አስታወቀ።

ሠራተኞቹ ለወራት ያህል ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ ይደርስባቸው እንደነበርም፣ የሚኒስትር መሥራ ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለሥልጣናቱ እንዳረጋገጡት፣ ከሩዋንዳ ጋር በምትዋሰነውና ከ፪ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በሚኖርባት ጎማ የመጀመራው የኢቦላ ህመምተኛ ተገኝቷል።

ባለሥልጣናት እንዳታወቁት፣ ህመምተኛው ከቤተምቦ በአውቶብስ ወደ ጎማ ይጓዝ የነበረ ፓስተር ሲሆን፣ ትናንት እሑድ ጎማ እንደደረሰ ወደ ኢቦላ መታከሚያ ማዕከል ተወስዷል።

የአውቶብሱ ሾፌርና መንገደኞች ደግሞ በዛሬው ዕለት ክትባት እንደተሰጣቸው የፈረንሳይ ዜና አውታር/AFP/ ዘግቧል።

ኢቢላ ኮንጎ ውስጥ፣ ከ1,600 በላይ ሰዎችን ገድሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG