በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃያ ሁለት ሚሊዮን ህጻናት የኩፍኝ ክትባት አላገኙም ተባለ


እአአ 2020 ከሃያ ሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ህጻናት የመጀመሪያቸውን የኩፍኝ ክትባት ሳይከተቡ መቅረታቸውን የዓለም የጤና ድርጅት እና የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ሲዲሲ ባወጡት ሪፖርት አስታወቁ።

የዓለም የጤና ድርጅት ባወጣው መግለጫ አሃዙ ባለፉት ሃያ ዓመታት ከፍተኛው መሆኑን አመልክቶ ለበሽታው መቀስቀስ የሚያመች አደገኛ ሁኔታ እንደሚደቅን አሳስቧል።

ባለፈው ዓመት የኩፍኝ ተያዦች ቁጥር በሰማኒያ ከመቶ ቀንሷል የሚሉ ሪፖርቶች እንዳሉ የጠቀሰው ድርጅቱ ሆኖም በዓመቱ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቅኝቶች በእጅጉ በማሽቆልቆሉ አሃዙ የሚያሳስት መሆኑን ገልጿል።

የዓለም የጤና ድርጅት የክትባት ዘርፍ ዲሬክተሯ ዶ/ር ኬት ኦብራያን በሰጡት ቃል ሁኔታው በዓለም ዙሪያ የኩፍኝ ወረርሺኝ የመቀስቀስ አደጋ እንዳለ የሚያመለክት መሆኑን አስታውቀዋል።

ሀገሮች ህዛባቸውን ፈጥነው ኮቪድ-19 ክትባቱን ፈጥነው ማዳረስ አንገብጋቢ እንደሆነ ገልጸው ሆኖም የሌሎች አስፈላጊ ክትባቶች መርኃ ግብሮች በማስቀረት እንዳይሆን ተጨማሪ ወጪ መመደብ ይኖርበታል ብለዋል። መደበኛ ክትባቶች መጠበቅ እና መጠናከር አለባቸው፥ አለበለዚያ አንዱን ገዳይ በሽታ በሌላ ገዳይ በሽታ የመቀየር አደጋ ይደቀናል ሲሉም አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG