በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ውስጥ የተጠለፉ ተማሪዎች ተለቀቁ


ሰሜን ናይጄሪያ ዲሚኒሢ ከተማ ከሚገኝ ቤቴል ባፕቲስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቅርቡ ከአንድ መቶ ሃያ በላይ ተማሪዎች የጠለፉት ታጣቂዎች ሃያ ስምንቱን እንደለቀቁ ተሰማ።

የቤተክርስቲያን አባቶች ልጆቹን ትናንት በትምህርት ቤቱ ለየወላጆቻቸው አስረክበዋል። ከሰማኒያ የሚበልጡት ተማሪዎች አሁንም በታጣቂዎቹ እጅ መሆናቸውን የቤተክርስቲያኒቱ ጉባዔ ፕሬዚደንት ገልጸዋል።

ከተጠለፉት ተማሪዎች መካከል እስካሁን ሰላሳ አራቱ ከጠላፊዎቻቸው አምልጠው ወይም ለቀዋቸው የተመለሱ ሲሆን የተቀሩት ይለቀቁ እንደሆን አልታወቀም፥ ታጣቂዎቹ ተማሪዎቹን ለመልቀቅ ለእያንዳንዱ ተማሪ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ዶላር ማስለቀቂያ መጠየቃቸው ተዘግቦ ነበር።

XS
SM
MD
LG