በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራና የአፋር አዋሳኝ ግጭት የ12 ሰው ሕይወት ቀጥፏል


በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን እና በአፋር ክልል የሚገኙ ሁለት ተጎራባች ቀበሌ ነዋሪዎች በየጊዜው በሚቀሰቀስ ግጭት ሲጋጩና ሲታረቁ ቢቆዩም አሁን ግን የ12 ሰዎች ሕይወትን ያጠፋ የከረረ ግጭት መፈጠሩን የሁለቱ አካባቢ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

የአማራና የአፋር አዋሳኝ ግጭት የ12 ሰው ሕይወት ቀጥፏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:03 0:00

ግጭቱ መሰረታዊ መፍትሔ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱም የሚጠፋው የሰው ሕይወትና በስጋት ቀያቸውን ጥለው የሚሰዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ይናገራሉ። የአካባቢው አስተዳደር አካላት እና የተመረጡ ሽማግሌዎች ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ጭምር ይገልፃሉ።

የአማራና የአፋር አዋሳኝ ግጭት የ12 ሰው ሕይወት ቀጥፏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:03 0:00

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ሶዶማ ቀበሌ በአፋር ክልል ውስጥ ከሚገኘው ጭፍራ ወረዳ ጋር ተጎራባች እንደሆነች የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልፃሉ። የሁለቱ ተጎራባች ነዋሪዎችም ለረጅም ጊዜ አብረው የኖሩና ተጋብተው የወለዱ ጎረቤታሞች ናቸው ይላሉ። ግን ደግሞ በየጊዜው በመካከላቸው ግጭት ይፈጠራል የሰው ሕይወት ይጠፋል ሽማግሌ ገብቶ ያስታርቃቸዋል እንደገና ደግሞ መልሰው እንደሚጣሉ ይናገራል።

ባለፈው ዕረቡ ሰኔ 28 የተከሰተው ግጭትም የዚህ አካል ነው ይላሉ። ከሁለቱም ወገን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለዚህ ዕለት ግጭት መነሻ የተለያየ ምክኒያትን ይሰጣሉ። “ቀድሞ ጥቃት የፈፀሙት እነሱ ናቸው” በማለት እርስ በእርስ ይካሰሳሉ። በሁለቱም ወገን የታየው ግን ከዕረቡ ሰኔ 28 እስከ አርብ ሐምሌ 1 ቀን ባደረጉት የሦስት ቀን ውጊያ የ12 ሰው ሕይወት መጥፋቱን ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG