በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቆይታ ከምን ልታዘዝ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ዳይሬክተርና መሪ ተዋናይ ጋር


ምን ልታዘዝ
ምን ልታዘዝ

“..እኛ እንደ ባለ ሞያ እንደ ወጣት ለሚፈጸሙ ነገሮች ቲፎዞ ልንሆን አንችልም። እገሌን እደግፋለሁ፣ እገሌን አስቀድማለሁ ሳይሆን .. የምናየው የኛ አገር ነው። ካፌው አገርን ነው የሚመስለው።..” መሪ ተዋናዩ ሚካኤል ታምሬ። “..ካፌ በተፈጥሮ ብዙ ሃሳብ ማስገባትና ማስወጣት ይፈቅዳል። እናም እንዲያ ማድረግ እፈልግ ነበር።” የትዕይንቱ ፀኃፊና ዳይሬክተር በኃይሉ ዋሴ።

“ሳታየር” (ስላቅ) ከተሰኘው የጥበብ ዘርፍ የሚመደብ፣ ፈጥኖም የብዙዎች የተከታታዮቹን ቀልብ ለመሳብ እና ተወዳጅነት ለማትረፍ ጭምር የታደለ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ነው - “ምን ልታዘዝ!”

በቀልዳ ቀልድ ለዛ የተዋበው ፖለቲካዊ ሥላቅ፣ በሥነ ጽሁፍ፥ በመድረክ አለያም በሥዕላዊ ሥራዎች አማካኝነት በማኅበረሠብ ውስጥ እየታዩ ያሉ ማኅበራዊ ህጸጾችንና ክስረቶችን ለመንቀስና ለመተቸት የሚሳል የጥበብ ዘዬ ነው። ፈታ-ዘና ብለው እንዲከተሉት የሚፈቅደው ይህ የጥበብ ዘዬ ታዲያ በአጫጭር ትዕይንቶች ይሞላ እንጅ ከኮርኳሪነቱ ጋር ቀልጠፍ ያለው ቅብብል ጭብጡን በቅጡ ከታዳሚው ከማድረስ አያገደውም።

ዘዬው በግለሰቦች የተፈጸሙ ድርጊቶችን ብቻ ሳይሆን በቡድኖች፣ አለያም በተቋማት፣ በአስተዳደርና በመንግስት ሲደረጉ የሚስተዋሉ ነገር ግን “ያልሆኑ” ጉዳዮች ይተቻል። ያጣጥላል።

ከምን ልታዘዝ ካፌ እንዝለቅ። የትዕይንቱ ጸሃፊና ዳይሬክተር በኃይሉ ዋሴ እና መሪ ተዋናዩ ሚካኤል ታምሬ እየጠበቁን ነው።

የመጀመሪያውን ክፍል ከዚህ ያድምጡ።

ቆይታ ከምን ልታዘዝ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ዳይሬክተርና መሪ ተዋናይ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:33 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG