በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱርክ ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን በድጋሚ ምርጫ አሸነፉ


የቱርክ ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን
የቱርክ ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን

ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት ቱርክን በፕሬዚዳንትነት የመሩት ሬሲፕ ታዪፕ ኤርዶዋን፣ ትላንት እሑድ በድጋሚ በተካሔደው የማጣሪያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በማሸነፍ፣ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አገሪቱን እንዲመሩ በድጋሚ ተመርጠዋል፡፡

ተቃዋሚዎቻቸው፣ የኑሮ ውድነቱን ቀውስ ተከትለው፣ ፕሬዚዳንቱን ከሥልጣን ለማውረድ ተስፋ አድርገው እንደነበር ተነግሯል፡፡

ይኹን እንጂ ኤርዶዋን፣ 52ነጥብ 2ከመቶ ድምፅ በማግኘት፣ 47ነጥብ 8 ከመቶ ድምፅ ያገኙትን ተፎካካሪያቸውን ከማል ኪሊች ዳሮግልን አሸንፈዋል፡፡

ኤርዶዋን ለደጋፊዎቻቸው በአሰሙት ንግግር፣ “አገራችንን ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት፣ በድጋሚ በሓላፊነት እንድመራ እምነት ለጣለብኝ እያንዳንዱ የአገሬ ሰው ምስጋናዬን አቀርባለኹ፤” ብለዋል::

ኪሊች ዳሮግል፣ የምርጫውን ውጤት ባይቃወሙም “በቅርብ ዓመታት ታሪክ ውስጥ የተካሔደ፣ “በጣም ፍትሐዊ ያልኾነ” ምርጫ ነው” ብለውታል፡፡

ኤርዶዋን፣ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ ያገኙት ድምፅ፣ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችላቸው ባለመኾኑ የትላንቱ የማጣሪያ ምርጫ መካሄዱ ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG