በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱርክ መንግስት ከኩርድ አማጽያን ጋር በሚያካሂደው ውግያ ለወታሃደራዊ ሃይሉ ሙሉ ስልጣን እንደሚሰጥ አስታወቀ


ፋይል- በኩርድ ታጣቂዎች የተካሄደ የቦንብ ጥቃት
ፋይል- በኩርድ ታጣቂዎች የተካሄደ የቦንብ ጥቃት

የቱርክ መንግስት ከኩርዲስታን አማጽያን ጋር በሚያካሄደው ውጊያ ለወታደራዊ ሀይሉ ሙሉ ስልጣን እየሰጠ ነው።

የሰብአዊ መብት ቡድኖች ግን ስልጣን ያለአግባብ የመጠቀም ክስ በሚሰማበት በአሁኑ ወቅት የጸጥታው ሀይል እንዲህ አይነት ሙሉ ስልጣን ሲያገኝ በማን አለብኝነት ለመንቀሳቀስ የሚያይስችለው ህጋዊ ፈቃድ ጨበጠ ማለት ነው በማለት ይነቅፋሉ። በተጨማሪም ጉዳዩ የቱርክንና የአውሮፓ ህብረት ግንኙነትን የባሰ ሊያሽክር ይችላል ተብሏል።

ከኩርድ አማጽያን ጋር የሚካሄደው ውጊያ እየተፋፋመ ባለበት በአሁኑ ወቅት የቱርክ ምክር ቤት ለሀገሪቱ ወታደራዊ ሃይል ዘርፈ ሰፊ የሆነ ስልጣን ለመስጠት እያሰላሰለ ነው። የቀረቡት ሃሳቦች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በአከባቢው የሲቪሎች ቁጥጥር እንዳይደረግባቸውና ወታደራዊው ሃይል መኖርያ ቤቶችን ካለፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዲፈትሽ መፍቀድን ያካተቱ ናቸው።

ፋይል-በኢስታንቡል ከተማ የተካሄደ ጥቃት
ፋይል-በኢስታንቡል ከተማ የተካሄደ ጥቃት

ሁማን ራይትስ ዋች በተባለው የሰብአዊ መብት ድርጅት የቱርክን ጉዳይ የሚያጠኑ ኤማ ሲንክሌር ዌብ በጣም የሚያሳስበው ነገር የጸጥታ ሃይሎች ህጋዊ ተጠያቂነትን የሚያከትም መሆኑ ነው ይላሉ።

“ህጉ እንደሚለው ማንኛውንም አይነት ምርመራ ለማካሄድ የመንግስት ባለስልጣኖች ፈቃድ ያስፈልጋል። ለወታደራዊው ሃይል ሙሉ ስልጣን መስጠት ማለት ግን “የማን አለብኝነት” ምልክት ማሳየት ማለት ነው። ስለሆነም ወታደራዊው ሃይል አይከሰስም፣ አይጠየቅም ማለት ነው።”

የቱርክ መንግስት በመጀመርያው የስልጣን ጊዜው የሀገሪቱ ወታደራዊ ሃይል ለሲቪል ባለስልጣኖች ተጠያቂ እንዲሆን የሚያደርግ ህግ አውጥቶ ነበር። አሁን ይህን ህግ ለመቀልበስ በመጣር ላይ ያለው ኩርዶች በሚበዙበት ደቡብ ምስራቅ ክፍል ከባድ ውጊያ በሚካሄድበት ወቅት ነው።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በተባለው አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት ጥናት የሚያካሄዱት እንድሪው ጋርድነር የጸጥታ ሀይሎች ከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣ እየፈጸሙ መሆናቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እየታዩ ናቸው ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዘይድ ራዓድ አል-ሁሴን የቱርክ የጸጥታ ሃይሎች ሲዘር በተባለች ከተማ ከመሬት በታች በሚገኝ ክፍል ውስጥ ተጠለው የነበሩ ሲቪሎችን በእሳት አጋይተው እንደገደሉ የሚጠቁሙ ተአማኒ ክሶች እንዳሉ ገልጸዋል። ቱርክ ክሱን በአጽንኦት አስተባብላለች። ይሁንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ክሱን እንዲመረምር አልፈቀደችም።

የቱርክ ፕረዚዳንት ረዚፕ ጠይብ ኢርደጎን የአውሮፓ ህብረት ከስልጣን ሊገለብጠኝ ይፈልጋል ሲሉ ከሰዋል። ቱርክ በአውሮፓ ህብረት አባልነት ትቀጥል እንደሆነ ለመወሰን ረፈረንደም ወይም ህዝበ-ውሳኔ ሊያካሄዱ እንደሚችሉም አመልክተዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG