በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት አንድ የቱርክ ረድኤት ሠራተኛ ተገደለ


ሞቃዲሾ፣ ሶማሊያ
ሞቃዲሾ፣ ሶማሊያ

ሶማሊያ ውስጥ የሚሠሩ አንድ ቱርካዊ የረድኤት ሠራተኛ ትናንት ሐሙስ ተገደሉ። ከአልቃይዳ ጋራ ግንኙነት ያለው የአልሻባብ ጣቂ ቡድን ለግድያው ኃላፊነት ወስዷል።

ጥቃቱ የተፈጸመው የቱርክ እና የሶማሊያ የርዳታ ሠራተኞችን እና ጠባቂዎቻቸውን ያሳፈረ ተሽከርካሪ ከሞቃዲሾ ከተማ ወጣ ብሎ ከሚገኝ መጠለያ ውስጥ ላሉ ተፈናቃዮች የምግብ ርዳታ ለማድረስ በመጓዝ ላይ ሳለ መሆኑ ተመልክቷል። መንገድ ዳር የተቀበረው ፈንጂ በአንደኛው ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩትን ቱርካዊ እና ሶማሊያዊ ባልደረባውን መግደሉን፤ እማኞች እና ፖሊሶች ገልጸዋል። ቬሬኒል የተሰኘው የቱርክ የረድኤት ድርጅት ኤክስ በተሰኘው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ባሰፈረው መረጃ እንዳመለከተው፤ በጥቃቱ የሶማሊያ ጽ/ቤቱ ተወካይ የነበሩት አብዱራህማን ዮሩክ መገደላቸውን አረጋግጧል።

የሶማሊያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ሻለቃ አብዲፈታህ አደን ሀሰን በበኩላቸው፣ "በረማዳን ጾም ላይ ለሚገኙ ችግረኞች ምግብ ለማድረስ በሚጓዙ የርዳታ ሠራተኞች ላይ የተፈጸመ" ሲሉ ጥቃቱን አውግዘዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG