በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም ትልቋ የፍልሰተኞች መጠጊያ ቱርክ ጫናው እየተሰማት ነው


በዓለም ትልቋ የፍልሰተኞች መጠጊያ ቱርክ ጫናው እየተሰማት ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:24 0:00

በዓለም ትልቋ የፍልሰተኞች መጠጊያ ቱርክ ጫናው እየተሰማት ነው

ቱርክ፣ ከሶሪያው የእርስ በርስ ጦርነት የሸሹ፣ ሦስት ሚሊዮን ሶሪያውያንን ጨምሮ፣ ከየትኛውም አገር የበለጠ ቁጥር ያላቸውን ፍልሰተኞች ቁጥር አስጠግታ እያኖረች ትገኛለች፡፡

ሥሉስ የተመረጡት የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ታዪፕ ኤርዶዋን፣ ሕዝባዊ ተቃውሞ እየበረታባቸው ቢኾንም፣ በዋናነት ከሶሪያ የሚመጡ አእላፋት ፍልሰተኞችን ተቀብለው በማሳደር ፖሊሲያቸው ጸንተዋል።

ወደ ቱርክ የተሰደዱት ዐያሌ ሶሪያውያን ፍልሰተኞች፣ ከቤት እና ከአገራቸው በላይ የኾነን ነገር አጥተዋል፡፡ በመጀመሪያው ስሙ ብቻ መጠራት የመረጠውን የ18 ዓመቱ ሰሚርን፣ የእርስ በርስ ጦርነቱ እግሩን ብቻ አይደለም ያሳጣው፤ ወላጆቹን ከአራት ወንድሞቹ እና እህቶቹ ጋራ ነጥቆታል፡፡

ይኹን እንጂ፣ “ለእግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰውና በሁሉም ነገር ረድተውኛል፤” የሚለው ሰሚር፣ “ሁሉም ነገር ጥሩ ነው፤ እግዜር የተመሰገነ ይኹን፡፡ እግሮቼን ቀስ በቀስ እያረታኹ እና እየተሻሻለ ሲመጣ፣ ዐዲስ ሰው ሠራሽ አካል ይቀይራሉ፡፡ ደረጃ በደረጃም መራመድ እጀምራለኹ፤” ሲል፣ እንደገና መራመድ እንደሚችል ተስፋ ያደርጋል፡፡

የኢስታንቡሉ የአጥንት ሕክምና ማዕከል የተቋቋመው፣ በቱርክ ሰብአዊ ርዳታ ተቋም እና በዓለም አቀፉ የዶክተሮች ማኅበር ነው፡፡ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀመውን ይህን ተቋም የሚመሩት፣ ዶር. ያሳር ታታር ናቸው፡፡ እጆቻቸው እና እግሮቻቸው የተቆረጡ ሶርያውያን፣ በከፍተኛ ቁጥር መኖራቸውን የሚናገሩት ታታር፣ “በተለይ፣ በበርሜል ቦምብ የደረሱ ቃጠሎዎች ትልቅ ፈተና ኾነውብናል፤” ይላሉ፡፡

በዚኽ ላይ ደግሞ፣ በምርጫው ሰሞን አንዳንድ ፖለቲከኞች፣ የፍልሰተኞችን ጉዳይ አጀንዳ አድርገውት ነበር፤”

“ወደ 2ሺሕ405 የሚደርሱ፣ እጅ እግራቸው የተቆረጡ ሰዎችን ረድተናል፡፡ እንዲሁም፣ በግምት ወደ 4ሺሕ የሚደርሱ፣ የሰው ሠራሽ እጆችንና እግሮችን ሠርተናል፤” የሚሉት ታታር፣ “ይህ ትልቅ ቁጥር ነው፡፡ በዚያ አጭር ጊዜ ውስጥ፣ ያን ያክል ሰው ሠራሽ እጆችንና እግሮችን መሥራት የሚችሉ ማዕከላት በጣም ትንሽ ናቸው፤” ብለዋል፡፡

በቱርክ እና በሶሪያ፣ ባለፈው የካቲት ደርሶ በነበረው ርዕደ መሬት፣ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ያጡ በርካታ ሰዎች፣ በማዕከሉ ላይ ተጨማሪ ሥራ ፈጥረዋል፡፡

ቱርክ፥ የኢራቅ እና የአፍጋን ፍልሰተኞችን ሳይጨምር፣ ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሶሪያ ፍልስተኞችን ታስተናግዳለች፡፡

ዛሬ፣ ፍልሰተኞችን የሚቃወሙ የግድግዳ ላይ ጽሑፎች፣ በቱርክ ውስጥ እየበዙ ነው፡፡ ከቱርክ የሰብአዊ ርዳታ ተቋም ሙስጠፋ ኦዝቤክ ይህንኑ ሲገልጹ፣ “ፍልሰተኞች በብዛት እየጎረፉ ከመኾናቸው ጋራ በተያያዘ፣ ማኅበረሰባዊ ጫናዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ በቱርክ ውስጥ በቅርቡ የታየው የኢኮኖሚ ችግር፣ ለዚኽ ተጨማሪ አስተዋፅኦ አድርጓል፤” ብለዋል፡፡

“በዚኽ ላይ ደግሞ፣ በምርጫው ሰሞን አንዳንድ ፖለቲከኞች፣ የፍልሰተኞችን ጉዳይ አጀንዳ አድርገውት ነበር፤” ሲሉም አክለዋል ኦዝቤክ፡፡

ባለፈው ግንቦት ወር በነበረው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ የፕሬዚዳንት ረሲፕ ታዪፕ ኤርዶዋን ተፎካካሪዎች ቢመረጡ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሶሪያውያን ፍልሰተኞችን፣ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ዝተው ነበር፡፡

ተንታኞች፣ የኤርዶዋን ድል፣ ለፍልሰተኞች ብቻ ሳይኾን፣ ቱርክ ፍልሰተኞችን እንድታስተናግድ፣ ገንዘብ ለሚከፍለው ለአውሮፓ ኅብረትም፣ እፎይታን እንዳስገኘ ይናገራሉ፡፡

በካዲር ሃስ ዩኒቨርስቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሰርሃት ጉቬንስ፣ “ኤርዶዋን በድጋሚ በተመረጡ ጊዜ፣ ምናልባት አውሮፓውያን እፎይታ ተሰምቷቸው ይኾናል፤” ይላሉ፡፡ ይህን ሲያስረዱም፣ “ምክንያቱም ያ ማለት፣ ለአውሮፓ ኅብረት መሪዎች፥ የፍልሰተኞች ውል በቦታው ሳይነካ ይቆያል፤ ተግባራዊነቱም ይቀጥላል፤” ብለዋል ጉቬንስ፡፡

ይኹን እንጂ፣ ፍልሰተኞችን አስመልክቶ፣ በቱርክ ሕዝብ ዘንድ ያለውን ቅሬታ እና አለመረጋጋት ኤርዶዋን ሳይገነዘቡ አልቀሩም፡፡ በመኾኑም አሁን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሶሪያውያን ፍልሰተኞች፣ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ኹኔታዎችን ስለማመቻቸት እየተናገሩ ነው፡፡

ኤርዶዋን፣ በሶሪያ፣ ከደማስቆ ቁጥጥር ውጭ የሚሠሩ የመኖሪያ ቤቶችን የግንባታ ሒደት ለማፋጠን ቃል ገብተዋል፡፡ ይህን ግብዣ ምን ያህሎቹ ይቀበሉታል የሚለው ግን፣ ውሎ አድሮ የሚታይ ይኾናል፡፡

XS
SM
MD
LG