በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱርክ ፍ/ቤት አሜሪካዊው ፓስተር እንዲለቀቁ የቀረበውን ጥሪ አልተቀበለም

አንድ የቱርክ ፍርድ ቤት አንድሪው ብራነን የተባሉት አሜሪካዊ ፓስተር እንዲለቀቁ የቀረበውን ጥሪ አልተቀበለም። የፓስተሩ መታሰር በቱርክና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የዲፕሎምሲ ጠብ ቀስቅሷል።

አንድ የቱርክ ፍርድ ቤት አንድሪው ብራነን የተባሉት አሜሪካዊ ፓስተር እንዲለቀቁ የቀረበውን ጥሪ አልተቀበለም። የፓስተሩ መታሰር በቱርክና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የዲፕሎምሲ ጠብ ቀስቅሷል።

ኢዝሙር ከተማ ያለው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብራንሰን በቁም እስር እንዲቆዩ በታችኛው ፍርድ ቤት የተበየነውን መደገፉን የቱርክ ሚድያና የታሳርው ጠበቃ ሰመ ሃላቨርት ገልፀዋል። በብራንሶን ላይ የተጣለው የጉዞ ዕገዳ እንዲነሳ የቀረበው ጥሪንም ከፍተኛው ፍርድ ቤት አልተቀበለም።

ዩናይትድ ስቴትስ በብራንሰን መያዝ ምክንያት በቱርክ ላይ አዲስ ማዕቀብ ብትጥል ቱርክ የአፃፋ ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ አንድ የቱርክ ሚኒስትር ከተናገሩ በኋላ ነው ብይኑ የፀደቀው። ፓስተሩ የተከሰሱት ፌቱላ ጉላን የተባሉ ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ እስላማዊ የሀይማኖት መሪን ይደጋፋሉ በሚል ነው። ቱርክ ፌቱላን አቻ አምና ተሞክሮ የከሸፈውን መፈንቅለ መንግሥት አቀንባብረዋል በሚል ትከሳለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG