ዋሺንግተን ዲሲ —
በድንገት ድራሹ እንደጠፋ የተነገረውን የሳዑዲ ጋዜጠኛ ጃማል ካሾጊንፍለጋ፣ ኢስታንቡል የሚገኘውን የሪያድ ቆንስላ ጽ/ቤት መበርበር እፈልጋለሁ ሲል፣ የቱርክ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠየቀ።
ይሁንና ቱርክ ላቀረበችው ጥያቄ እስካሁን ከሳዑዲ በኩል የተሰጠ መልስ የለም። ይልቁንም፣ የሳዑዲ ባለሥልጣናት፣ የቱርክ ጥርጣሬ፣ መሰረተ ቢስ ነው ሲሉ ነው የሚሰሙት።
የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልመን ባለፈው ሳምንት በተናገሩት ቃል ግን፣ የደረሰበት በጠፋው የ59 ዓመቱ ጋዜጠኛ ጃማል ካሾጊ ጉዳይ ሪያድ አንዳች የምትደብቀውም ሆነ የምሰጋበት ነገር ስለሌለ፣ በቱርክ መንግሥት በኩል ያቀረበውን ጥያቄ ትቀበላለች ማለታቸው አይዘነጋም።
የቱርክ ባለሥልጣናት፣ ጋዜጠኛው፣ ሀገራቸው ውስጥ በሚገኘው በኢስታንቡሉ የሳዑዲ ኤምበሲ ውስጥ እንደተገደለ ይጠራጠራሉ። ግቢው ይፈተሽልን የሚለውን ጥያቄም ከዚሁ ጥርጣሬ የመነጨ መሆኑ ይታወቃል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ