በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

25 ሺሕ ሶሪያውያን ወደ ሃገራቸው መመለሳቸውን ቱርክ አስታወቀች


ባሻር አል አሳድ ከሥልጣን ከተወገዱ ወዲህ ከቱርክ ከ25 ሺሕ በላይ ሶሪያውያን ወደ ሃገራቸው መመለሳቸውን የቱርክ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከ13 ዓመታት በፊት በሶሪያ ጦርነቱ መፈንዳቱን ተከትሎ፣ ሦስት ሚሊዮን የሚሆኑ ሶሪያውያን ወደ ቱርክ ተሰደው ነበር። የሶሪያውያኑ በዛች ሃገር መገኘት ለረሽፕ ታይፕ ኤርዶዋን መንግሥት ችግር እንደነበር የኤ ኤፍ ፒ ዘገባ አመልክቷል።

ባለፉት 15 ቀናት ወደ ሶሪያ የተመለሱት ሰዎች ቁጥር ከ25 ሺሕ ማለፉን የቱርክ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

አንካራ ከአዲሶቹ የሶሪያ መሪዎች ጋራ የቅርብ ግንኙነት እንዳላትና ሶሪያውያን በፈቃደኝነት በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ማተኮሯን፣ እንዲሁም በደማስቆ የሥልጣን ለውጥ በመኖሩም አብዛኛዎቹ ስደተኞች ወደ ሃገራቸው እንደሚመለሱ ቱርክ ተስፋ እንደምታደርግ ሪፖርቱ አመልክቷል።

ቱርክ ከ12 ዓመታት በፊት በጦርነቱ ፈርሶ የነበረውን ኤምባሲዋን አሳድ ከስልጣን በተወገዱ በሳምንቱ እንደገና ከፍታለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG