በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዚዳንት ትራምፕ የእሥራኤል ዋና ከተማናት ዕውቅና በመቃወም በኢስታንቡል ስብሰባ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ኢየሩሳሌምን የእሥራኤል ዋና ከተማ ማድረጋቸውን በመቃወም፣ በእስላማዊው ዓለም የሚገኙ ሃያ ሁለት መሪዎች ኢስታንቡል ውስጥ መሰባሰባቸው ተሰማ።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ኢየሩሳሌምን የእሥራኤል ዋና ከተማ ማድረጋቸውን በመቃወም፣ በእስላማዊው ዓለም የሚገኙ ሃያ ሁለት መሪዎች ኢስታንቡል ውስጥ መሰባሰባቸው ተሰማ።

የመሪዎቹ ስብሰባ የተጀመረው፣ ከፕሬዚደንት ትራምፕ ውሣኔ ጋር በተያያዘ፥ መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ውጥረቱ ባየለበት ወቅት መሆኑ ነው።

ስብሰባውን ያዘጋጀው፣ ሃምሳ ሰባት አገሮች በአባልነት የሚገኙበት (ኦ አይ ሲ) የእስልምና ጉባዔ ድርጅት ነው።

ይህን ጉባዔ በአሁኑ ወቅት ቱርክ በሊቀመንበርነት የምትመራ ሲሆን፣ አስቸኳይ ስብሰባውን የጠሩትም ፕሬዚደንቱ ራሲፕ ታዪፕ ኤርዶዋን ናቸው።

ኤርዶዋን በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ባሰሙት ንግግር፣ “ለዓለማቀፍ ህግና ለፍትህ ከፍተኛ ግምት ያላቸውን እነዚህን መሪዎች ለስብሰባ ስንጋብዝ፣ የኢየሩሳሌምን የፍልስጥኤም ዋና ከተማነት እንዲገነዘቡ በማሰብ ነው” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG