በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱርክ ኃይሎች ሦርያ ውስጥ ጥቃት አካሄዱ


የቱርክ ኃይሎች ሰሜናዊ ሦርያ ውስጥ በዛሬው ቀን ጥቃት ማካሄዳቸው ተነገረ።

የቱርክ ኃይሎች ሰሜናዊ ሦርያ ውስጥ በዛሬው ቀን ጥቃት ማካሄዳቸው ተነገረ።

ይህ የኩርድ ሚሊሽዎችን ከአፍሪን አካባቢ ጨርሶ ለማስወጣት የተወሰደው እርምጃ በቶሎ እንደሚጠናቀቅ፣ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

የኩርድ ሚሊሽያም በበኩሉ፣ ከቱርክ ኃይሎች ጋር ዛሬ ሰኞ ሰሜናዊ ምዕራብ አፍሪን ውስጥ ግጭት መካሄዱን አመልክቷል።

የቱርክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር መህመት ሲምሴክ አጠር ባለ ገለፃቸው፣ ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃው፣ ቱርክን ከሽብር አደጋ የማዳን አካል ነው ብለዋል።

አንካራ፣ አፍሪንን የሚቆጣጠው “ዋይፒጂ” ሚሊሽያ ቱርክ ውስጥ ከአማፅያን ጋር ግንኙነት አለው በማለት ትከሳለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG