በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ የግድያ ምርመራ ባፋጣኝ መጠናቀቅ አለበት ሲሉ ኤርዶዋን አሳሰቡ

ፎቶ ፋይል፡-የሳዑዲ አረቢያው ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ
ፎቶ ፋይል፡-የሳዑዲ አረቢያው ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ

ኑሮው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የነበረው የሳዑዲ ዓረቢያው ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ ኢስታንቡል ውስጥ በሚገኘው በሪያድ ቆንስላ ጽ/ቤት ግቢ እንዲገደል ትዕዛዝ የሰጠው ማን እንደሆን፣ ሳዑዲ ዓረቢያ መናገር አለባት ሲሉ፣ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋን ጥሪ አቀረቡ።

ኑሮው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የነበረው የሳዑዲ ዓረቢያው ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ ኢስታንቡል ውስጥ በሚገኘው በሪያድ ቆንስላ ጽ/ቤት ግቢ እንዲገደል ትዕዛዝ የሰጠው ማን እንደሆን፣ ሳዑዲ ዓረቢያ መናገር አለባት ሲሉ፣ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋን ጥሪ አቀረቡ።

ኤርዶዋን ለፓርላማ አባሎቻቸው ዛሬ ማስከኞ ባሰሙት ቃል፣ ዣማል ኻሾግዢ የግድያ ምርመራ ባፋጣኝ መጠናቀቅ አለበት ሲሉም፣ ኤርዶዋን አሳስበዋል።

ይቅርታ የሌለው ነገር ነው የሚሉት የቱርኩ መሪ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙት 18 የሳዑዲ ተጠርጣሪዎች በአስቸኳይ እንዲላኩም ጠይቀዋል። እስካሁን የት እንዳለ ያልታወቀው የሟቹ ጋዜጠኛ አስከሬን የሚገኝበትን ስፍራ በማፈላለግም፣ ሳዑዱ እንድትተባበር ቱርክ ጠይቃለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG