በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“አሜሪካና አውሮፓ በእስራኤል ላይ በቂ ግፊት እያደረጉ አይደሉም” ቱርክ


ፎቶ ፋይል፦ የቱርኩ ፕሬዝደንት ረችፕ ታይፕ ኤርዶዋን
ፎቶ ፋይል፦ የቱርኩ ፕሬዝደንት ረችፕ ታይፕ ኤርዶዋን

አሜሪካና የአውሮፓ ሃገራት እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት እንድትፈጽም በቂ ግፊት በማድረግ ላይ አይደሉም ሲሉ የቱርኩ ፕሬዝደንት ረችፕ ታይፕ ኤርዶዋን ትላንት እሁድ ተናግረዋል።

ሐማስ ተኩስ ለማቆም የቀረበውን ሃሳብ መቀበሉን ተከትሎም እስራኤል በጋዛ ላይ ጥቃት መፈጸሟ በቀጠለበት ሁኔታ የምዕራቡ ዓለም ለእስራኤል የሚሰጠውን ድጋፍ መቀጠሉን ቱርክ ነቅፋለች፡፡

ቱርክ ከእስራኤል ጋራ ያላትን የንግድ ግንኙነት ማቆሟን እና ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፉ ችሎት በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን ክስ እንደምትቀላቀል መወሰኗን አስታውቃለች፡፡

ኢስታንቡል ውስጥ ለእስልምና ምዑራን ንግግር ያደረጉት ኤርዶዋን፣ “በቃጣር እና ግብፅ የቀረበውን የተኩስ ማቆም ሃሳብ ሐማስ ቢቀበልም፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ መንግስት ግን ጦርነቱን ማቆም አይፈልግም” ሲሉ ተደምጠዋል።

የቱርኩ የደህንነት ሹም ኢብራሂም ካሊን ትላንት እሁድ ዶሃ ላይ ከሐማስ መሪዎች ጋራ በተኩስ ማቆም እና የሰብዓዊ ዕርዳታ ለጋዛ በሚቀርብበት ጉዳይ ላይ መነጋገራቸውን የሃገሪቱ የደህንነት ምንጮች አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG