በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱርክ መንግሥት ለሶማልያ ወታደሮች ጦር መሣሪያ ሰጠ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የቱርክ መንግሥት ለሶማልያ ወታደሮች ጦር መሣሪያ መስጠቱን፣ የሶማልያው መከላከያ ሚኒስትር መሐመድ ዓሊ ሀጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ሶማልኛ አገልግሎት አረጋገጡ።

የቱርክ መንግሥት ለሶማልያ ወታደሮች ጦር መሣሪያ መስጠቱን፣ የሶማልያው መከላከያ ሚኒስትር መሐመድ ዓሊ ሀጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ሶማልኛ አገልግሎት አረጋገጡ።

ሚንስትሩ ከቪኦኤ ሶማልኝእ አገልግሎት ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቱርክ መንግሥት ከሁለት ሣምንታት በፊት ካደረገው የጦር መሣሪያ ስጦታው በተጨማሪ፣ ወታደሮችን ሞቅዲሾ ውስጥ ለማሰልጠንም ቃል መግባቱን አውስተዋል።

ሚንስትሩ መሐመድ ሀጋ አክለውም፣ ስጦታው የሚያካትተው እንደ ጠመንጃ የመሳሰሉ አነስተኛ ጦር መሣሪያዎችን ሲሆን፣ ያም ተመድ ሶማልያ ላይ የጣላቸውን ከባድ ጦር መሣሪያዎችን አይጭርም ብለዋል።

የቱርክ መገናኛ አውታር እንዳረጋገጠውም፣ ለሶማልያ የተሰጡት ጦር መሣሪያዎች ቱርክ ሥር የሆኑ እንደ /MPT-76/ ጠመንጃዎች ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG