በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱርክ በደረሰው የመሬት ርዕደት የሞተው ሰው ቁጥር ሠላሳ ዘጠኝ ደረሰ


ባለፈው ሳምንት ቱርክ ውስጥ በደረሰው ከባድ የመሬት ርዕደት ሳቢያ የሞተው ሰው ቁጥር ሠላሳ ዘጠኝ መድረሱን የሀገሪቱ የአደጋ ደራሽ መስሪያ ቤት አስታወቀ።

ኤላዚግ የተባለውን የቱርክ ምስራቃዊ ክፍለ ግዛት ዓርብ ማታ ያናወጠው በመለኪያው መሳሪያ በሪክትር ስኬል ስድስት ነጥብ ስምንት ያስመዘገበ ርዕደት ነው። አራት ሺህ የሚሆኑ ፈጥኖ ደራሽ ሰራተኞች በከባዱ ቅዝቃዜ ሁኔታ ውስጥ ተሰማርተው በመሳሪያ አማካይነት ፍርስራሹን ሲቆፍሩ ቆይተዋል።

ባለሥልጣናት እንዳሉት ሰባ ስድስት ህንጻዎች ወድመዋል ፤ በመቶውዎች የተቆጠሩ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

እስካሁን አርባ አምስት ሰዎችከፍርስራሹ ውስጥ በህይወት ማውጣት መቻሉን ነው ባለሥልጣናት የገለጹት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG