በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱርክ ከእስላማዊ መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ጥቃት ሊያደርሱ ሲሉ መያዟን አስታወቀች


የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ያርሊካያ
የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ያርሊካያ

ቱርክ ከእስላማዊ መንግስት ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን እና ጥቃት ለማድረስ ሲያሴሩ እንደነበር የገለፀቻቸውን 29 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሏን የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ያርሊካያ ዛሬ አርብ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ ኤክስ በመባል በሚጠራው የማህበራዊ መገናኛ ሚዲያ ላይ ባጋሩት ፅሁፍ፣ "ዘመቻ ጀግኖች 37" በተሰኘ እንቅስቃሴ የተያዙት ተጠርጣሪዎች ኢስታምቡል በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እና ምኩራቦች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር አቅደው እንደነበር ገልፀዋል።

የደህንነት ምንጮችን ጠቅሶ የዘገበው አናዶሉ የተሰኘ የቱርክ መንግስት የዜና አገልግሎት በበኩሉ፣ ከ29ኙ እስረኞች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሌሎች ሦስት ሰዎችም በዘመቻው መያዛቸውን ዘግቧል። ሦስቱ ግለሰቦች የእስላማዊ መንግስት አባል መሆናቸውን እና አንካራ በሚገኘው የኢራቅ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲዘጋጁ መያዛቸውንም ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።

በጥቅምት ወር መጀመሪያ የኩርድ ታጣቂዎች በአንካራ የመንግስት ህንፃ አቅራቢያ ቦምብ ካፈነዱ በኃላ፣ ባለስልጣናት በእስላማዊ መንግስት እና በኩርድ ታጣቂዎች ላይ የሚያካሂዱትን ዘመቻ አጠናክረው ቀጥለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG