በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካዊው በቱርክ ዋሻ ውስጥ ችግር ገጠመው


አሜሪካዊው በቱርክ ዋሻ ውስጥ ችግር ገጠመው
አሜሪካዊው በቱርክ ዋሻ ውስጥ ችግር ገጠመው

የቱርክ እና ዓለም አቀፍ የዋሻ ውስጥ የአደጋ ግዜ ሰራተኞች በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል 1 ሺሕ ሜትር በላይ ጥልቀት ካለው ዋሻ ውስጥ ገብቶ የቀረውን አሜሪካዊ ለማውጣት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።

የዋሻ ውስጥ ጉዞ አዘውታሪው እና የ40 ዓመት ዕድሜ ያለው ማርክ ዲኪ፣ በደቡብ ቱርክ የሚገኘውን እና 1 ሺህ 276 ጥልቀት ያለውን ዋሻ ካርታ ለመሥራት በሚሞክርበት ወቅት፣ 1 ሺሕ ሜትር አካባቢ እንዳለ በመታመሙ መንቀሳቀስ አልቻለም። የአንጀት መድማት ስለገጠመው በራሱ መውጣት እንዳልቻለ ታውቋል።

የሠለጠነ የዋሻ ውስጥ ተጓዥ እና እርሱም የዋሻ ውስጥ አደጋ አዳኝ እንደሆነ የተነገረለት ማርክ ዲኪ፣ በዓለም አቀፍ የዋሻ አደጋዎች ወቅት ቀድሞ በመድረስ ይታወቃል ተብሏል።

የአውሮፓ የዋሻ ውስጥ አደጋ ደራሽ ማኅበር የህክምና ኮሚቴው ጸሃፊ ነውም ተብሏል።

ከቱርክ እና ከ5 ሀገራት የተውጣጡት የዋሻ ውስጥ የአደጋ ግዜ ሰራተኞች፣ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ግለሠቡን ማውጣት እንደሚጀምሩ ይጠበቃል ሲል አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG