በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ፕሬዚዳንት ቱርክን እየጎበኙ ነው


የቱርክ ፕሬዚዳንት ጠይብ ኤርዶጋን፣ ለእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ኼርዞክ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል አድርገውላቸዋል፤ አንካራ፣ ቱርክ እአአ መጋቢት 9/2022
የቱርክ ፕሬዚዳንት ጠይብ ኤርዶጋን፣ ለእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ኼርዞክ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል አድርገውላቸዋል፤ አንካራ፣ ቱርክ እአአ መጋቢት 9/2022

የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ኼርዞክ በዛሬው ዕለት የሁለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ቱርክ መግባታቸው ከአስር ዓመት በላይ ቀዝቅዞ የቆየው ግንኙነታቸው መሻሻል የማሳየቱ ምልክት ነው ተብሏል፡፡

የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት አንካራን የሚጎበኙት ቱርክ እስራኤል በጋዛ ያደረግችውን ጥቃት በመቃወም እኤአ በ2018 ኤባሲዋን ከእስራኤል ማስወጣቷ ከተነገረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ከአካባቢው ፖለቲካ እየተነጠለች መሆንዋ የሚያሳስባት ቱርክ፣ በሥልጣን ዘመናቸው በሙሉ የፍልስጤማውያን ደጋፊ በመሆን የሚታወቁት የቱርክ ፕሬዚዳንት ጠይብ ኤርዶጋን ቱርክ የሃማስ መጠጊያና መንቀሳቀሻ ስፍራ እየሆነች ነው የሚለውን የእስራኤልን ስጋት አስመልክቶ ጥያቄ እንደሚቀርብባቸው ተገምቷል፡፡

ይሁን እንጂ ባለሙያዎች ቱርክ በመካከለኛው ምስራቅ ልትጫወት የምትችለው ሚና የተረዳችው እስራኤል በተለይም የጋራ ሥጋታቸው በሆነው የኢራን የኒውክለር ሥምምነት ጉዳይ ላይ አብረው የመስራት ፍላጎት እንደሚኖራቸው አመልክተዋል፡፡ ዋሽንግተንም በሁሉቱ አገሮች መካከል የታየውን መቀራረብ ተስፋ የሚያሳድር መሆኑን ገልጻለች፡፡

አሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተነታኞች ግን የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ጉብኘት በቱርኩ ፕሬዚዳንትና በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ወደፊት ይደረጋል ለተባለው ግንኙነት የመጀመሪያው እምርጃ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG