ዋሽንግተን ዲሲ —
ቱርክ በኮቪድ 19 ሳቢያ ለሁለት ዓመታትተ ቋርጦ የነበረውን የአፍሪካ ቱርክ ጉባኤን በነገው እለት በቱርክ ዋና መዲና ኢስታሙብል ውስጥ እንደምታካሄድ ተገለጸ፡፡ ጉባኤው ከነገ አርብ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ድረስ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ተነገሯል፡፡
በአፍሪካ ውስጥ ትልቅ የንግድ ግብይት እንዲኖራት በመስራት ላይ የምትገኘው ቱርክ አፍሪካ ውስጥ ከ30 በላይ ኤምባሲዎችን መክፈቷ ሲነገር የቱርክ ፕሬዚዳንት ታይፕ ኤርዶጋንከ እኤአ 2003 ጀምሮ 28 ጊዜያት አፍሪካን የጎበኙ መሪ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
የመንግሥት ዘገባዎች እንደሚሳዩት ቱርክ እኤአ ከ2003 ጀምሮ ከአፍሪካ ጋር ያላት የንግድ ልውውጥ በአምስት እጥፍ አድጎ 25 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡