በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱኒዝያ አብዮትና ትምህርቱ


የቱኒዚያው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ፕሬዚዳንቱን ቤን አሊን ከሃገር ጥለው እንዲሸሹ በማስገደድ ብቻ አላበቃም፡፡

“የሕዝቡን ኃብት ሠርቀው ወደ ውጭ አሽሸዋል” ሲል የከሰሣቸው የሃገራቸው የፍትሕ ሚኒስቴር በተገኙበት እጃቸው ተይዞ እንዲሰጠው የእሥር ማዘዣ አውጥቷል፡፡

ይህ በሥራ እጦት፣ በዋጋ ንረትና በውስጥ ችግር ሣቢያ ቱኒዚያ ውስጥ የተቀጣጠለው አብዮት ወደሌሎችም በአምባገነኖች የሚመሩ የአፍሪካ ሃገሮች እየተዛመተ ይመስላል፡፡

“ዴሞክራሲ በተግባር” ዝግጅታችን በግብፅ የታየውንና ዋና ከተማይቱን ካይሮን አጨናንቆ የዋለውን ትዕይንተ ሕዝብ አንዱ የመነጋገሪያ ነጥብ አድርጎታል፡፡

የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ሰሎሞን ክፍሌ አቶ ጆሃር መሐመድን ጋብዟል፡፡ አቶ ጆሃር በዩናይትድ ስቴትስ የታወቀው የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ሲሆኑ ከሁከት ነፃ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ሥልጠና ይሰጣሉ፡፡ ምክርም ይለግሣሉ፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG