በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱኒዚያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ


ቱኒዚያ ውስጥ ትላንት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተካሂዷል። ከ24 በላይ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈውበታል። ኦፊሴላዊ ያልሆነ የምርጫው ውጤት ባመለከተው መሰረት ከገዢው ክፍል ጋር ብዙም ትስስር የላቸውም የተባሉ ሁለት ተወዳዳሪዎች እየመሩ መሆናቸው ተዘግቧል።

ቱኒዚያ ውስጥ ከስምንት ዓመታት በፊት ጃዝሚን የሚል ስያሜ የተሰጠው አብዮት ከተካሄደ ወዲህ ነፃ ምርጫ ሲካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከሰባት ሚልዮን በላይ ዜጎች የመምረጥ መብት እንዳላቸው ተገልጿል።

ለመምረጥ በመቻልዋ የተደሰተችው የ19 ዓመት ዕድሜ የኮሌጅ ተማሪ ዮማ ኤል ቤና የተሻሉ የሚመስሉኝን ሞሩን እመርጣለሁ ብላለች።

ዐብደል፡ፋታህ ሞሩ የተባለው ለዘብተኛ እስላማዊ ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ ናቸው። ባለፈው ሀማሌ ወር የሞቱትን የ 92 ዓመት ዕድሜ ፕሬዚዳንት ቦታ ለመያዝ ነው የሚወዳደሩት። ለፕሬዚዳንትነት ከሚወዳደሩት መካከል ሁለት ሴቶች ይገኙባቸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG