በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶሪያና ቱኒዝያ ከአስር ዐመታት በኋላ የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን አደሱ


የሶሪያ ፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ
የሶሪያ ፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ

ቱኒዥያ በደማስቆ አዲስ አምባሳደሯን መመደቧን ተከትሎ ሶሪያ በቱኒዚያ ኤምባሲዋን እንደምትከፍት የሶሪያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

ቱኒዚያ ከሶሪያ ጋር እኤአ ከ2012 ጀምሮ ለአስር ዓመታት ያቋረጠችውን የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን በማደስ የኋለኛዋ ከአረብ አገር ስትሆን ውሳኔዋ የአካባቢው ሀገሮች ጦርነት ከበጣጠቃት ሶሪያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመቀጠል ከያዙት አዲስ ጥረት ጋር የተያያዘ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በተለይም እኤአ የካቲት 6 በቱርክና ሶሪያ ከደረሰው ከባድ የርዕደ መሬት አደጋ ወዲህ፣ እንዲሁም በቻይና ሸምጋይነት ሳኡዲ አረብያና ኢራን ግንኙነታቸውን ለማደስ ከተስማሙ ወዲህ ጥረቱ እየጨመረ መምጣቱን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

የሶሪያ ፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ ተቃዋሚዎችን በኃይል በመጨፍለቃቸው እና በኋላም ወደ የርስ በርስ ጦርነት በተቀየረው እኤአ የ2011ዱ ህዝባዊ ዓመጽ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ባደረሱት ጭፍጨፋ ሶሪያን ብዙዎች የአረብ አገሮች አግልለዋት ቆይተዋል፡፡

የአረብ ሊግ ካባረራት በኋላም ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል፡፡ እየጨመረ የመጣውን ዓለም አቀፍ እዳ ለመቀነስ አይኤምኤፍ “ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ” እያወጣ መሆኑንም ኃላፊ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ጥብቅ የፋይናንስ ቁጥጥር “ከፍተኛ የወለድ መጠን ጭማሪ ሳይኖር” የገንዘብ ፖሊሲው የዋጋ ግሽበት እንዲቀንስ ያደርገዋል በህብረተሰቡም ውስጥ እንዲሁ የተመጣጠነ የዋጋ ክፍፍል እንዲኖር ይፈቅዳል” ሲሉ የአይኤምኤፍ የመንግሥታት ገቢ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊው ቪቶር ጋስፐር ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG