በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱኒዥያ ፕሬዚዳንት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ምርጫ እንደማይካሄድ አስታወቁ


ቱኒዥያ
ቱኒዥያ

በዚህ ሳምንት ምክር ቤቱን የበተኑት የቱኒዥያ ፕሬዚዳንት ሳዪድ ካዪስ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ምርጫ እንደማይካሄድ ትናንት ማታ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ይህ በፕሬዚዳንቱ አብዛኛውን የህገ መንግሥቱን የዲሞክራሲ መርሆች ወደጎን ትተው በግላቸው ወደፊት መግፋቱን እንደቀጠሉ አመላካች መሆኑ ተገልጹዋል።

በሀገሪቱ ያሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ጠንካራው የሰራተኛ ማኅበር ፓርላማውን የበተኑት ፕሬዚዳንት ባፋጣኝ ምርጫ ማካሄድ እንዳለባቸው ህገ መንግሥቱን እየጠቀሱ ጠይቀዋል። ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው "ይህን የህገ መንግሥት ትርጉዋሜ ከየት እንዳመጡት አላውቅም” ብለዋል።

ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ባወጡት መግለጫ ፕሬዚዳንቱ ፓርላማውን መበተናቸው እና እርምጃቸውን በመቃወም በተካሄደ ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የምክር ቤት አባላትን በህግ እንዲጠየቁ ሊያደርጉ ነው የሚሉ ሪፖርቶች በጥልቅ አሳስበዋናል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG