በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱኒዚያ ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩት ፖለቲከኛ የ12 ዓመት እስር ተፈረደባቸው


ፎቶ ፋይል፦ በእስር ላይ የሚገኙት የፕሬዚዳንት ዕጩ አያቺ ዛሜል ፖስተር
ፎቶ ፋይል፦ በእስር ላይ የሚገኙት የፕሬዚዳንት ዕጩ አያቺ ዛሜል ፖስተር

በቱኒዚያ የሚገኝ ፍ/ቤት፣ የተቃዋሚው ፓርቲው ፕሬዝደንታዊ ዕጩ ላይ የ12 ዓመት እስር ቅጣት አስተላልፏል።

የድምፅ ሰጪዎችን ይሁንታ በሚያሰባስቡበት ጊዜ ማጭበርበር ፈፅመዋል የተባሉት የተቃዋሚው ዕጩ አያቺ ዛሜል፣ በመጪው እሁድ በሚደረገው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ላይ ተፎካካሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ ጠበቃቸው አስታውቀዋል።

ውድድሩን በመምራት ላይ ያሉትና አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝደንት ካይስ ሳያድ በእ.አ.አ 2019 ወደ ሥልጣን የመጡ ሲሆን፣ ፓርላማውን አፍርሰው በሌላ የተገደበ ሥልጣን ባለው ሕግ አውጪ አካል ተክተውታል። ፕሬዝደንቱ የፍትህ ሥርዓቱን በመጠቀም ተቀናቃኞቻቸውን እያሰወገዱ ነው የሚል ትችት ይቀርብባቸዋል።

አያቺ ዛሜል ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ ነበር ሰነድ አጭበርብረዋል በሚል በቁጥጥር ሥር የዋሉት፡፡ ከፕሬዝደንቱ ጋራ እንዲወዳደሩ በሃገሪቱ ምርጫ ቦርድ ፈቃድ ከተሰጣቸው ሁለት እጩዎች አንዱ ነበሩ። ሌሎቹ ተወዳዳሪዎችን መንግስት አግዷል።

ቅጣቱ “ፍትሃዊ ያልሆነና ቧልት” ነው ሲሉ ጠበቃቸው ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG