በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ቢያንስ ዘጠኝ ፍልሰተኞች ሞቱ

ፎቶ ፋይል፦ የቱኒዚያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች በቱኒዚያ እና ጣሊያን መካከል ባለው ባሕር ላይ ሲዘዋወሩ፣ በትንሽ ጀልባ ተጨናንቀው የተጫኑ እና ወደ አውሮፓ እየሸሹ ያሉትን ፍልሰተኞችን ለማዳን ጅልባቸውን አስጠግተው ይታያል፣ እአአ ነሃሴ 10/2023
ፎቶ ፋይል፦ የቱኒዚያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች በቱኒዚያ እና ጣሊያን መካከል ባለው ባሕር ላይ ሲዘዋወሩ፣ በትንሽ ጀልባ ተጨናንቀው የተጫኑ እና ወደ አውሮፓ እየሸሹ ያሉትን ፍልሰተኞችን ለማዳን ጅልባቸውን አስጠግተው ይታያል፣ እአአ ነሃሴ 10/2023

በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈ የዘጠኝ ፍልሰተኞችን አስከሬን ማግኘታቸውን የሃገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ከደረሰው አደጋ የተረፉ 27 ፍልሰተኞችን መታደጋቸውንና የስድስት ፍልሰተኞች ፍለጋ መቀጠሉን ባለሥልጣናቱ ጨምረው አስታውቀዋል።

የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ አውሮፓ በማቅናት ላይ የነበሩት ፍልሰተኞች ጀልባ በመስጠም ላይ መሆኗን ያየ አሳ አስጋሪ ለባለሥልጣናት ሁኔታውን በማሳወቁ የማዳን እንቅስቃሴ መጀመሩ ተነግሯል።

ስምንት ሴቶችን ጨምሮ 42 ፍልሰተኞች ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት የተነሱ መሆናቸውም ታውቋል።

በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ብቻ በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ ከ600 እስከ 700 የሚደርሱ ፍልሰተኞች ሕይወት በጀልባ አደጋ ምክንያት ማለፉን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG