በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢንዶኔዥያ በደረሰው የሱናሚ ማዕበል የሞቱ ሰዎች ቁጥር 373 ደረሰ


ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከትናንት በስተያ በደረሰው የሱናሚ ማዕበል የሞቱ ሰዎች ቁጥር ዛሬ ወደ 373 ማሻቀቡን የሃገሪቱ የአደጋ አያያዝ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከትናንት በስተያ በደረሰው የሱናሚ ማዕበል የሞቱ ሰዎች ቁጥር ዛሬ ወደ 373 ማሻቀቡን የሃገሪቱ የአደጋ አያያዝ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የባንተን ክፍለሃገርን የባሕር ጠረፍ አካባቢ ማዕበሉ ከመታ ከሁለት ቀናት በኋላም እስከ ዛሬ ከመቶ በላይ ሰው የት እንዳለ እንደማይታወቅና ቢያንስ 1 ሺህ 459 ሰው መጎዳቱን የኢንዶኔዥያ የአደጋ ሥራ አመራር ብሄራዊ ቦርድ አመልክቷል።

ሱንዳ የሚባለው ሠርጥ አካባቢ ያጥለቀለቀው የከትናንት በስተያው ሱናሚ 681 መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ ወደ አንድ ሺህ የሚሆኑ ሕንፃዎችንና ግንባታዎችን መጉዳቱ ወይም ማውደሙ ተገልጿል።

ሱናሚውን በአካባቢው ጊዜ ከትናንት በስተያ ከምሽቱ 3 ሰዓት ተኩል አካባቢ የቀሰቀሰው በአቅራቢያው ከግማሽ ሰዓት ቀደም ብሎ አናክ ክራካቶአ የሚባለው ተራራ ላይ የፈነዳ እሣተ-ገሞራ ሳይሆን እንዳልቀረ የሃገሪቱ የሚቲኦሮሎጂ፣ የአየር ንብረትና የከርሰምድር ጥናት መሥሪያ ቤት ጠቁሟል።

የሱናሚው መቀስቀስ ትክክለኛ ምክንያት ምን እንደሆነ እየተጣራ መሆኑን ለቪአኤ የገለፁት የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ከፍንዳታው ጋር የባሕር ውስጥ የመሬት መናድም ሳይደርስ እንዳልቀረና እርሱም ለሱናሚው መቀስቀስ ተጨማሪ አስተዋፅዖ ሳያበረክት እንደልልቀረ አመልክተዋል።

ለደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን በትዊተር ባወጡት መልዕክት ያሳወቁት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “አሜሪካ ከእናንተ ጋር ነች” ብለዋል።

በአደጋው የተጎዱ የአሜሪካ ዜጎች ስለመኖራቸው ወይም አለመኖራቸው ለጊዜው መረጃ እንደሌለው ያሳወቀው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ “ይሁን እንጂ አስፈላጊ በሆነው ሁሉ ልናግዝ ዝግጁ ነን” ብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG