በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ሬክስ ቲለርሰንን ከሥራ አስወገዱ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን እና በዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ የስለላ አገልግሎት /ሲአይኤ/ ሥራ አስኪያጅ ማይክ ፖምፕዮ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን እና በዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ የስለላ አገልግሎት /ሲአይኤ/ ሥራ አስኪያጅ ማይክ ፖምፕዮ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን ከሥራ አስወግደው በዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ የስለላ አገልግሎት /ሲአይኤ/ ሥራ አስኪያጅ ማይክ ፖምፕዮ እንደሚተኳቸው ታውቋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን ከሥራ አስወግደው በዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ የስለላ አገልግሎት /ሲአይኤ/ ሥራ አስኪያጅ ማይክ ፖምፕዮ እንደሚተኳቸው ታውቋል።

አንድ ከፍተኛ የዋይት ሃውስ ባለሥልጣን ዛሬ በተናገሩት መሰረት ቲለርሰን በአሁኑ ወቅት ከሥራ የተወገዱት ከሰሜን ኮርያ ጋር ለሚደረገው ንግግርና ስለሚካሄዱት የተለያዩ ድርድሮች አዲስ ቡድን ለማዘጋጀት ሲባል ነው።

“ሬክስ ቲለርሰንን ለአገልግሎታቸው እናመስግናለን። ጊና ሃስፔን የመጀመርያዋ ሴት የ/ሲአይኤ/ CIA ሥራ አስኪያጅ ይሆናሉ። ሁላችሁም እንኳን ደስ ያላችሁ ሲሉ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ በትዊተር መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቲለርሰን በሥራቸው የመቆየት ዓላማ እንደነበራቸውና ከሥራው እወገዳለሁ ብለው እንዳላሰቡ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስቲቭ ጎልድስተይን ገልጸዋል። ቲለርሰን የተባረሩበት ምክንያት እንዳላወቁም ባለሥልጣኑ አክለዋል።

ትረምፕና ቲለርሰን ለወራት ያህል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲጋጩ እንደቆዩ በአንድ ሁኔታ ቲለርሰን ፕረዚዳንቱን “ሞሮን” ማለት ደደብ ብለዋቸው እንዳነበር ተዘግቧል። ቲለርሰን ይህን ብለው እንደሆነ በተዳጋጋሚ በጋዜጣኞች ተጠይቀው መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG