ዋሺንግተን ዲሲ —
አንድ ከፍተኛ የዋይት ኃውስ ባለሥልጣን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማግለጫ የትረምፕ የኢሞግረሽን ዕቅድ ከፍተኛ ትምህርትና ክኅሎት ባላቸው ላይ እንደሚያተኩር አስገንዝበዋል።
የትረምፕ ዕቅድ ግሪን ካርድ የተባለው ለህጋዊ ፍልሰተኞች የሚሰጠው የነዋሪነት ፈቃድ ብዛት በዓመት 1.1 ሚልዮን ይሆናል። ይሁንና ትኩረቱ ተቀይሮ ቀዳሚነት የሚሰጠው ከፍተኛ ትምህርትና ክኅሎት ላላቸው እንጂ ለቤተሰብ ማገናኘትና ለሰብዓዊ ጉዳይ አይሆንም፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ