ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እየተዳከመ ያለውን የሀገሪቱን መሠረተ ልማት ለማስተካከል የሚያስችላቸውንና ለብዙ ጊዜ ሲጠበቅ የቆየውን የ$1.5 ትሪሊዮን ዕቅዳቸውን ዛሬ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ በአሜሪካ መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ የባቡር ሐዲዶችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ለ10 ዓመት ይረዳል ከተባለው የበጀች ዕቅድ ውስጥ $200 ቢሊዮን ለፈደራል በጀት ሌላውን $1.3 ትሪሊዮን ደግሞ ለልዩ ልዩ ግዛቶች እንደሚመደብ ታውቋል።
ይህ ሳምንት በተለይ ለመሠረተ ልማት ከፍተኛ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ሳምንት መሆኑን ነው፣ ፕሬዚዳንት ትረምፕ በትዊተር የገለጹት።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ