በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትረምፕ እንዲካሄድ የጠየቁት ወታደራዊ ትርዒት ለቀጣዩ ዓመት ተላለፈ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እንዲካሄድ የጠየቁት ወታደራዊ ትርዒት ለቀጣዩ ዓመት መተላለፉን፣ የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እንዲካሄድ የጠየቁት ወታደራዊ ትርዒት ለቀጣዩ ዓመት መተላለፉን፣ የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

“እኛ መጀመሪያውኑም ለመጪው ኅዳር 2018 ነበር ያቀድንው፣ አሁን ግን ወደ 2019 ዓ.ም መተላለፉን ተስማምተንበታል” ሲሉ፣ የፔንታገን መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሮቤርት ማኒንግ ተናግረዋል።

የትርዒት መካሄጃ ጊዜው መተለፉ ይፋ የሆነው፤ ወጪው ከ$12 ሚሊዮን ወደ $92 ሚሊዮን ማሻቀቡ ከተዘገበ በኋላ ነው።

መከላከያ ሚኒስትሩ ጂም ማቲስ፣ ለትርዒቱ መነሻ የሚሆን መመሪያ እንደሰጡ ገልፀው፣ ስለ ወጭ ግን ምንም የሚያውቁት ዝርዝር እንደሌለ ነው የተናገሩት፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG