ትላንት ሰኞ ቃለመሐላቸውን ፈጽመው ኋይት ሐውስን የተረከቡት ፕሬዚደን ዶናልድ ትረምፕ በአስተዳደራቸው የመጀመሪያ ቀን በርከት ያሉ ማስፈጸሚያ ትዕዛዞች ፈርመዋል። ዋና ዋና በሆኑ ጉዳዮች ከፈረሟቸው የማስፈጸሚያ ትዕዛዞች መካከል የስደተኞችን ጉዳይ እና የኃይል ልማትን የሚመለከቱ ይገኙባቸዋል።
በበዓለ ሲመት ንግግራቸው ትረምፕ የዩናይትድ ስቴትስን ግዛት እስከማርስ እናሰፋዋለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።
አኒታ ፓወል ከኋይት ሐውስ ያጠናቀረችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም