ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ በተከራየው የዕቃ መጫኛ መኪና ሥምንት ሰዎችን ሆን ብሎ ገጭቶ በመግደል የተወነጀለው የኡዝቤክሳታኑ ተወላጅ በሞት መቀጣት አለበት በሚለው አቋማቸው ፀንተዋል።
ኪዩባዋ ጉዋንታናሞ ቤይ ወደሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ እሥር ማዕከል ይላክ ያሉትን ግን ተወት እያደረጉ ናቸው።
“የኒውዮርኩን አሸባሪ ጉዋንታናሞ ብንልከው በወደድኩ፣ ነገር ግንያ ሂደት በዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት ቢዳኝ ከሚወስደው ጊዜ ጋር ሲነፃፀር ረጅም ጊዜ ይወስዳል” ሲሉ ዛሬ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።
“አሰቃቂውን ወንጀሉን በፈፀመበት ቦታ መቆየቱ ተገቢ ይሆናል። የሃያ ዘጠኝ ዓመቱ ሳይፉሎ ሳይፖቭ የፍርድ ሂደት ተፋጥኖ ይከናወን፡፡ የሞት ቅጣት ይፈረድበት” ብለዋል።
ሳይፖቭ ትናንት ረቡዕ ክስ ተመስርቶበታል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ