ዋሺንግተን ዲሲ —
ዛሬ ከዋይት ኃውስ ቤተመንግሥት ከመነሳታቸው በፊት “በመሳርያ ቁጥጥር ላይ በጣም ጥሩ በሆነ ውሳኔ ላይ እንደርሳለን” ብለው ነበር። ይሁንና መሳርያ የሚገዙትን ሰዎች የጀርባ ታሪክ ማጥናት ያስፈልጋል የሚል እምነት ቢኖራቸውም ስለመሳርያ ዕገዳ የፖለቲካ ፍላጎት የለም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
ፕሬዚዳንቱ የሚያሰሙት ፀረ ፍልሰት ልፈፋ በሀገሪቱ ለሚታየው መርዛማ ድባብ አስተዋፅዖ አድርጓል። ግለሰቦች በገበያ ማዕከላት፣ በሙዚቃ ትርዒት፣ በመዝናኛ ቦታዎችና በዕምነት ቦታዎች የጅምላ ግዲያ እንዲፈፅሙ አበረታቷል የሚለውን ነቀፌታ ፕሬዚዳንት ትረምፕ አስተባብለዋል።
ከባለቤታቸው ቀዳማዊት እምቤት ጋር ሆነው አይሮፕላን ላይ ከሳፈራቸው በፊት “ንግግር ሰዎችን ያቀራርባል እንጂ አይከፋፍልም” ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ