ባለፈው ቅዳሜ በቀድሞው ፕሬዝድነት ዶናልድ ትረምፕ ላይ በተቃጣው የግድያ ሙከራ ወቅት ሕይወቱን ያጣው የቀድሞ የእሳት አደጋ መከላከያ ሃላፊ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ በፔንሲልቬኒያ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።
ሟች ኮሪ ኮምፔራቶር በተኩሱ ወቅት ባለቤቱን እና ሴት ልጁን ከጥይት ሲከልል እንደነበር ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
በግድያ ሙከራው ጆሯቸው የቆሰለው ትረምፕ በቀብር ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደማይገኙ ታውቋል። ምክንያቱ ደግሞ ፕሬዝደንታዊ የጥበቃ ቡድኑ (ሲክረት ሰርቪስ) በሥፍራው ያለው የደህንነት ሁኔታ ስላሳሰበው ነው ተብሏል።
በጥቃቱ ወቅት ሌሎች ሁለት ሰዎች ክፉኛ ተጎድተው በአሳሳቢ ሁኔታ የነበሩ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን በአንጻራዊ የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።
መድረክ / ፎረም