በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በአፍጋኒስታን ያሉ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ወደሃገራቸን መመለስ አለባቸው አሉ


ፎቶ፦ በአፍጋኒስታን የሚገኝ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደር
ፎቶ፦ በአፍጋኒስታን የሚገኝ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደር

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የያዝነው የአውሮፓውያን ዓመት በመጭው ኅዳር ወር ከማብቃቱ በፊት በአፍጋኒስታን ያሉትን የአሜሪካ ወታደሮችን ሁሉ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ እንደሚፈልጉ ትናንት ተናግረዋል።

ጥቂቶቹ በአፍጋኒስታን የቀሩት ጀግና ሴቶችና ወንዶች እስከ መጭው የገና በዓል ባለው ጊዜ ወደ ሃገራቸው መመለስ አለባቸው ሲሉ ትረምፕ ትናንት በትዊተር ገልፀዋል። በሀገሪቱ ታሪክ ረጅም የተባለውን ጦርነት በአፍጋኒስታን ላይ የተጀመረው እአአ በ2001 ዓ.ም ነበር፤ ከ19 ዓመታት በፊት - የዐልቃይዳ አሸባሪዎች በኒው ዮርክ ከተማና በዋሺንግተን ዲሲ ያደረሱትን ጥቃት ለመበቀል ነበር ጦርነቱ የተከፈተው።

የአሜሪካው ወረራ ያኔ ሥልጣን ላይ የነበረውን ታሊባን ከሥልጣን ለማስወገድ ትሏል። እአአ መስከረም 11 ቀን በአሜሪካ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ያስተባበረው ኦሳማ ቢንላደንና የሽብር መረቡ የመሸጉት አፍጋኒስታን ውስጥ እንደነበር ይነገራል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ የአሜሪካ ወታደሮች እስከ ዓመቱ ማብቂያ ላይ ባለው ጊዜ በአፍጋኒስታን ለማስወጣት ማሰባቸው በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገው የሰላም ሥምምነት ይጠቅማል ሲል ታሊባን አሞግሶታል።

ታሊባን ፕሬዚንዳት ትረምፕ ያሉትን አውንታዊ እርምጃ ብሎታል።

እአአ ባለፈው የካቲት 29፣ ለ19 ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት ለማብቃት ሲባል ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የፈረመውን የሰላም ሥምምነት ተግባራዊ ማድረግ ይኖራል ብሎታል።

XS
SM
MD
LG