በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትረምፕ የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ህግ እንዲሻሻል አሳሰቡ

በህገወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የገቡ ህፃናትን ከመባረር ለማዳን ያለው ዕድል እየጠበበ በመሆኑ፣ እልህ አስጨራሹ የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ህግ እንዲሻሻል የምክር ቤት አባላት መፍትሔ እንዲፈልጉ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አሳሰቡ።

በህገወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የገቡ ህፃናትን ከመባረር ለማዳን ያለው ዕድል እየጠበበ በመሆኑ፣ እልህ አስጨራሹ የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ህግ እንዲሻሻል የምክር ቤት አባላት መፍትሔ እንዲፈልጉ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አሳሰቡ።

ሪፖብሊካኖችም ሆኑ ዴሞክራቶች ስምምነት ላይ መደረስ እንዳለበት ይስማማሉ በማለት የገለጹት ፕሬዚዳንት ትረምፕ፣ «ከብዙ ዓመታት በኋላ በዚህ እንቆቅልሽ በሆነው የዳካ ጉዳይ ወደ አንድ አስማሚ ነጥብ ብንደርስ እንደምን ድንቅ በሆነ ነበር?» ሲሉም ተናግረዋል።

ትረምፕ በዛሬ የማክሰኞ ትዊተር መልዕክታቸውም፣ ከአሁን በኋላ ሌላ አጋጣሚ የሌለውና የመጨረሻው ዕድል መሆኑንም አመልክተዋል።

ባለፈው ዓመት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ይህን ወጣት ስደተኞችን ከመባረር የሚከላከለው ዳካ ውድቅ እንዲሆን ማድረጋቸውና፣ ምክር ቤቱም እስከ መጋቢት 26 ቀን ህግ እንዲያወጣለት ቀነ ቀጠሮ መስጠታቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG