በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ከሩስያ ጋር የተደረገ መመሳጠር የለም አሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ፕሬዚዳንታዊ ውድድር ከሩስያ ጋር ግንኑኘት የነበረው እንደሆነ ከሚመረምሩት ልዩ ካውንስል ሮበርት ሙለር ጋር ተገናኝተው የሚነጋገሩበት ሁኔታ ያለ እንደማይመስላቸው ትራምፕ ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ፕሬዚዳንታዊ ውድድር ከሩሰያ ጋር ግንኑኘት የነበረው እንደሆነ ከሚመረምሩት ልዩ ካውንስል ሮበርት ሙለር ጋር ተገናኝተው የሚነጋገሩበት ሁኔታ ያለ እንደማይመስላቸው ትራምፕ ተናግረዋል።

ትረምፕ ትላንት ይህን ያሉት ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ ጋር ተገናኝተው ከተነጋገሩ በኋላ በተካሄደው ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ ነው።

ከሩስያ ጋር የተደረገ መመሳጠር የለም። ስለሆንም ሙለር ከሳቸው ጋር ሊነጋገሩ የሚችሉበት ሁኔታ አይኖርም ብለዋል። ከሩስያ ጋር የተመሳጠሩት ዲሞክራቶች ናቸው ሲሉም አክለዋል።

በሚካሄደው ምርመራ መሰረት የሙለር መርማሪ ቡድን ፕሬዚዳንት ትረምፕን ሊያነጋግር እንደሚፈልግ ሙለር ለፕሬዚዳንቱ ጠበቆች አመላክተዋል። ትራምፕ የምርመራውን ሂደት “የዲሞክራቶች ተንኮል ነው” ብለዋታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG