በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ፍርሃት፣ ትረምፕ በዋይት ኃውስ" አዲስ መጽሃፍ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥትን በትርምስና በሥራ አግባብ ጉድለት የታመሰ አድርጎ በሚያቀርበው መጽሃፍ ላይ እየወረዱበት ነው። የተሳሳቱ ወሪዎችን ለመካለከል ሲባል የመቅጫ ህጎቹ መለወጥ አለባቸው የሚል ሃሳብ ዛሬ አቅርበዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥትን በትርምስና በሥራ አግባብ ጉድለት የታመሰ አድርጎ በሚያቀርበው መጽሃፍ ላይ እየወረዱበት ነው። የተሳሳቱ ወሪዎችን ለመካለከል ሲባል የመቅጫ ህጎቹ መለወጥ አለባቸው የሚል ሃሳብ ዛሬ አቅርበዋል።

Fear: Trump in the White House
Fear: Trump in the White House

“አንድ ሰው በፈጠራ ወሬ ላይ የተመሰረት መጽሃፍ ወይም ጽሁፍ አውጥቶ የአንድን ሰው ገፅታ በተቃራኒው አድርጎ ሲያቀርብና ዋጋ ሳያስከፍለው ሲቀር አይሳዝንም? ሲሉ ትረምፕ በትዊተር አስተላልፈዋል። “ፍርሃት፣ ትረምፕ በዋይት ሀውስ” በሚል ርዕስ ባብ ውድዋርድ አዲስ መጽሃፍ አሳትመዋል።

ከመጽሃፉ ተቀነጫጭበው ትላንት የውጡ ክፍሎች ትረምፕ በዓለም ዙርያ ስላለው ሁኔታ ያላቸው ዕውቀት በአደገኛ ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያል። የዋይት ኃውስ ሠራተኞችም በውስጣዊ ቂም በቀል የተበከሉ ናቸው ይላል።

የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛው ውድዋርድ እአአ በ1974 ሪቻርድ ኒክሰን ከፕሬዚዳንትነት ሥልጣናቸው እንዲወርዱ አስተዋጾዖ ያደረገ እንደመሆኑ መጠን ለዲሞክራቶች እየሰራ ሳይሆን አይቀርም በማለት ሪፖብሊካዊው ፕሬዚዳንት ትረምፕ ነቅፈዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG